1. የሰማያትና የምድር፣ በውስጣቸውም ያሉት ሁሉ አፈጣጠር በዚህ ሁኔታ ተከናወነ።
2. እግዚአብሔር ይሠራ የነበረውን ሥራ በስባተኛው ቀን ላይ ፈጽሞ ነበረ፤ ስለዚህ ከስራው ስራ ሁሉ በሰባተኛው ቀን ዐረፈ።
3. እግዚአብሔር ሰባተኛውን ቀን ባረከው። ቀደሰውም፤ ካከናወነው የመፍጠር ሥራው ሁሉያረፈው በሰባተኛው ቀን ነውና።
አዳምና ሔዋን
4.እግዚአብሔር አምላክ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረ ጊዜ የተከናውኑት እንደዚህ ነበረ።
እግዚአብሔር አምላክ ሰማያትንና ምድርን ሲፈጥር
5. የሜዳ ቡቃያ ገና በምድር ላይ አልታየም፤ የሜዳ ተከልም ገና አልብቀለም፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር አምላክ በመሬት
ላይ ገና ዝናብ አላዘንበም ነበረ፤ ምድርንም የሚያለማ ሰው አልነበረም።
6. ነገር ግን ውሃ ከመሬት እየመነጨ የምድርን ገጽ ያረሰርስ ነበረ።
7. እግዚአብሔር አምላክ ከምድር ዐፈር ወስዶ ሰውን አበጀው፤ በአፍንጫውም ይሕይወት እስንትንፋስ እፍ አለበት፤ ሰውም
ሕያው ነፍስ ሆነ።
8. እግዚአብሔር አምላክ በምስራቅ፤ በዔደን የአትክልት ስፍራ አዘጋጀ፤ ያበጀውንም ሰው በዚያ አኖረው።
9. እግዚአብሔር አምላክ ለዐይን የሚያስደስ ለምለም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ከምድር አበቀለ፤ በአትክልቱ ቦታ
መልካም የሕይወት ዛፍ ነበረ፤ እንዲሁም መልካመና ክፉን መልየት የሚያስችለው የዕውቀት ዛፍ ነበረ።
10. የአትክልት ስፍራውን የሚያጠጣ ወንዝ ከዔደን ይፈስ ነበር፤ ከዚያም በአራት ተከፍሎ ይወጣ ነበር።
11. የመጀመርያው፤ ወርቅ በሚገኝበት ብሓዊላ ምድር ዙርያ ሁሉ የሚፈሰው የፌሶን ወንዝ ነው።
12. ኤውላጥ ምርጥ የሆነ ወርቅ፤ መልካም መዐዛ ያለው ከርቤና የከበረ ድንጋይ በሚገኙበት ምድር ነው።
13. ሁለተኛው፤ በኢትዮጰያ ምድር ዙርይ ሁሉ የሚፈስው የግዮን ወንዝ ነው።
14. ሦስተኛው፣ ከአሦር በስተ ምስራቅ የሚፈሰው የጤግሮስ ወንዝ ሲሆን፣ አራተኛው የኤፍራጥስ ወንዝ ነው።
15. እግዚአብሔር አምላክ ሰውን ወስዶ እንዲያለማትና እየተንከበከበ እንዲጠብቃት በዔደን የአትክልት ስፍራ አስቀመጠው።
16. እግዚአብሔር አምላክ ሰውን እንዲህ በማለት አዘዘው፤ "በአትክልት ስፍራው ውንጥ ከሚገኝ ከማንኛውም ዛፍ ፍሬ ትበላለህ።
17. ነገር ግን መልካምና ክፉን ከሚያሳውቀው ዛፍ አትብላ፤ ምክንያቱም ከእርሱ በበላህ ቀን በርገጥ ትሞታለህ።"
18. ከዚህ ቦኋላ እግዚአበሔር አምላክ "ሰው ብቻውን መሆኑ መልካም አይደለምና የሚስማማውን ረዳት አበጅለታለሁ" አለ።
19. እግዚአብሔር የዱር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ከምድር ሰርቶ ነበር፤ ለእያንዳንዳቸውም ምን ስም እንደሚያወጣላቸው ለማየት
ወደ አዳም አመጣቸው። አዳም ሕይወት ላላችው ፍጡራን ሁሉ ያወጣላችው ስም መጠርያቸው ሆነ።
20. ስለዚህ አዳም ለከብቶች፣ ለሰማይ ወፎች፣ ለዱር አራዊት ሁሉ ስም አወጣላችው።
ይሁን እንጂ ለአዳም ተስማሚ ረዳት አልተገኘለትም ነበረ።
21. እግዚአብሔር አምላክም በአዳም ላይ ከባድ እንቅልፍ ጣለበት፤ አንቀላፍቶም ሳለ ከጎድኑ አንዲት ዐጥን ዎስዶ፣ ስፍራውን በስጋ ሞላው።
22. እግዚአብሔር አምላክም ከአዳም የወሰዳትን ዐጥንት ሴት አድርጎ ሠራት፤ ወደ አዳምም አመጣት።
23. አዳምም አንዲህ አለ። "እነሆ፤ የህች ዐጥንት ከዐጥንቴ፣
ሥጋም ከስጋዬ ናት።
ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል።
24. ስለዚህ ሰው ከአባቱና ከእናቱ ተለይቶ ከሚስቱ ጋር ይጣመራል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።
25. አዳምና ሚስቱ፣ ሁለቱም እራቁታችውን ነበሩ፣ ይሁን እንጂ እይተፋፈሩም ነበር።