የ ፍጥረት አጀማመር
1. በመጀመርያ እግዚአብሔር ስማያትንና ምድርን ፈጠረ:፡
ምድርም ቅርጽ የለሽና ባዶ ነበረች::
2. የምድርን ጥልቅ ስፍራ ሁሉ ጨለማ
ውጦት ነበረ:፡ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውሆች ይረብብ ነበረ።
3. ከዚያም እግዚአብሔር "ብርሃን ይሁን" አለ፤ ብርሃንም ሆነ::
4. እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደ ሆነ አየ፤ ብርሃኑን ከጨለማ ለየ።
5.እግዚአብሔርም ብርሃኑን "ቀን" ጨለማውን "ሌሊት" ብሎ ጠራው::
መሽ፡ ነጋም፡ የመጀመርያ ቀን።
6. እግዚአብሔርም "ውሃን ከውሃ የሚለይ ጠፈር በውሆች መካከል ይሁን" አለ::
7.ስለዚህ እግዚአብሔር ጠፈርን አድርጎ ከጠፈሩ በላይና ከጠፈሩ በታች ያለውን ውሃ
ለየ።
8. እግዚአብሔር ጠፈርን "ሰማይ" ብሎ ጠራው። መሽ፤ ነጋም፤ ሁለተኛ ቀን።
9. ከዝያም እግዚአብሔር "ከሰማይ በታች ያለው ውሃ በአንድ ስፍራ ይከማች፤
ደረቁ ምድር ይገለጥ" አለ፤ እንዳለውም ሆነ።
10. እግዚአብሔር ደረቁን ምድር "የብስ"፤ በአንድንት የተሰበስበውን ውሃ፤ "ባሕር"
ብሎ ጠራው። እግዚአብሔር ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ።
11. እግዚአብሔር "ምድር ዕፅዋትንም፤ እንደየወገናቸው ዘር የሚስጡ ተክሎችንና
በምድር ላይ ዘር ያዝሉ ፍሬ የሚያፈሩ ዛፎችን እንደየወገናቸው ታብቅል" አለ፤
እንዳለውም ሆነ።
12. ምድር ዕፅዋትን እንደየወገናቸ ዘር የሚስጡ ተክሎችንና በውስጣቸው ዘር
ያለባቸው ፍሬ የሚያዘሩትን ዘሮ በየ ወገኑ አበቀለች። እግዚአብሔርም ይሕ መልካም
እንደሆነ አየ።
13. መሽ ነጋም፤ ሥስተኛ ቀን።
14. ከዚያም እግዚአብሔር "ቀኑን ከለሊት እንዲለዩ፤ የዓመት ወቅቶች፤ ቀናትና ዓመታት
የሚጀምሩበትንም እንዲያመለክቱ፤
15. ለምድር ብርሃን የሚሰጡ ልዩ ልዩ ብርሃናት በሰማይ ይሁኑ" አለ። እንዳለውም ሆነ።
16. እግዚአብሔር ለምድር ብርሃን ይሰጡ ዘንድ ሁለት ታላላቅ ብርሃናት አደረገ፤ ታላቁ ብርሃን
በቀን እንዲሠለጥን፤ ታናሹ ብርሃን በሌሊት እንዲሠለጥን አደረገ። እንዲሁም ከዋክብትን አደረገ።
17. ለምድር ብርሃን እንዲሰጡ እንዚህን በሰማይ ጠፈር አኖራቸው።
18. ይኽውም በቀንና በሌሊት እንዲሠለጥኑ ብርሃኑን ከጨለማ እንዲለዩ ነው።
እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደሆን አየ።
19. መሸ ነጋም፤ አራተኛ ቀን።
20. እግዚአብሔር "ውሆች ሕይወት ባላቸው በሕያዋን ፍጡራን ይሞሉ፤ ወፎች ከምድር በላይ
በሰማይ ጠፈር ይብረሩ አለ።
21. በዚህ መሠረት፤ እግዚአብሔር በባሕር ውስጥ የሚኖሩ ታላላቅ ፍጡራንን፤ በውሃ ውስጥ
የሚርመሰመሱ ሕይውት ያላቸው ነገሮች እንደየውገናችው እንዲሁም ክንፍ ያላቸውን ውፎች ሁሉ
እንደየውገናችው ፈጠረ። እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደሆነ አየ።
22.እግዚአብሔርም "ብዙ ተባዙ፤ የባሐርን ውሃ ሙሏት፤ ወፎችም በምድር ላይ ይብዙ" ብሎ
ባረካቸው።
23. መሸ፤ ነጋም፤ አምስተኛ ቀን።
24. እግዚአብሔር "ምድር ሕያዋን ፍጡርንን እንደየወገናቸው፤ ከብቶችን፤ በምድር ላይ የሚሳቡ
ፍጡራንና የዱር እንስሳትን እያንዳንዱን እንድ ወገኑ ታስገኝ" አለ፤ እንዳለውም ሆነ።
25. እግዚአብሐር የዱር እንስሳትን እንድየወገናችው፤ ከብቶችን እንደየወገናቸው፤ እንዲሁም በመድር
ላይ የሚሳቡ ፍጡራንን እንድየወገናችው አደረገ። እግዚአብሔር ይህ መልካም እንደሆነ አየ።
26. እግዚአብሔር "ሰውን በመልካችን፤ ባምሳላችን እንሥራ፤ በባሕር ዓሶች፤ በሰማይ ወፎች፤ በከብቶች
፤ በምድር ሁሉ ላይ፤ እንዲሁም በምድር ላይ በሚሳቡ ፍጡራን ሁሉ ላይ ስልጣን ይኑራቸው" አለ።
27.ስለዚህ እግዚአብሔር ሰውን በራሱ መልክ ፈጠረው፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት
አርጎ ፈጠራቸው።
28. እግዚአብሔር፤ "ብዙ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሏት፤ ግዟትም፤ የባሕርን ዓሥች፤ የ ሰማይን ወፎች፤ እንዲሁም
በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትን ሕያዋን ፍጡራንን ሁሉ ግዟቸው" ብሎ ባረካቸው።
29. እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤"በምድር ላይ ያሉትን ዘር የሚሰጡ ተክሎችን ሁሉ
በፍሬያችው ውስጥ ዘር ያለባቸውን ዛፎች ሁሉ ምግብ የሁንላችሁ ዘንድ
ሰጥቻችኋለሁ።
30. እንዲሁም ለምድር አራዊት ሁሉ፣ ለሰማይ ወፎች ሁሉ፣ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱ ሕያውያን
ፍጡራን ሁሉ ማንኛውም ለምለም ተክል ምግብ እንዲሆናቸው ሰጥቻለሁ" እንዳለውም ሆነ።
Working progress....Do you want to contribute? email me