Wednesday, February 3, 2010

ኦሪት ዘፍጥረት ፣ ምዕራፍ 3

የሰው ውድቀት
1. እባብ እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠራቸው የዱር አራዊት ሁሉ ተንኮለኛ ነበረ።
ሴቲቱንም "ቤእርግጥ እግዚአብሔር `በአትክልቱ ስፍራ ካሉ ዛፎች ከማናቸውም እንዳትበሉ` ብሎአልን?" አላት።
2. ሴቲቱም እባቡን እንዲህ አለችው፡ "በአትክልቱ ስፍራ ካሉት ዛፎች ፍሬ መብላት እንችላለን፤
3. ነገር ግን እግዚአብሔር በአትክልቱ ስፍራ መካክል ከሚገኘው ዛፍ ፍሬ እንዳትብሉ፤ እንዳትነኩትም፤ አለበለዚያ
ትሞታላችሁ" ብሎአል።"
4. እባቡም ሴቱትን እንድህ አላት፤ "መሞት እንኳ አትሞቱም;
5. ከፍሬው በበላችሁ ጊዜ ዐይናችሁ እንድሚከፈትና መልካምና ክፉን በማወቅ እንደ እግዚአብሔር እንደምት ሆኑ
እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው።"
6. ሴቲቱ የዛፉ ፍሬ ለመብል መልካም፣ ለዐይን የሚያስደስትና ጥበብንም ለማግኘት የምያጓጓ እንደ ሆነ ባየች ጊዜ፣
ከፍሬው ወስዳ በላች፤ ከእርሷም ጋር ለነበረው ለባሏ ሰጠችው፤ እርሱም በላ።
7. የሁለቱም አይኖች ተከፈቱ፤ ዕርቃታቸውን መሆናቸውንም ተገነዘቡ። ስለዚህ የበለስ ቅጠል ሰፍተው አገለደሙ።
8.ቀኑ መሸትሸት ሲል፣ እግዚአብሔር አምላክ ባትክልቱ ስፍራ ሲምላልስ አዳምና ሔውን ድምፁን ሰምተው ከእግዚአብሔር አምላክ
ፊት በዛፎች መካከል ተሸሸጉ። እግዚአብሔር አምላክ አዳምን ተጣርቶ፣ "የት ነህ" አለው።
10. አዳምም፣ "ድምፅህን ባትክልቱ ስፍራ ሰማሁ፤ ዕራቁቴን ስለ ሆንሁ ፈራሁ፤ ተሸሸግሁም" ብሎ መለሰ።
11. እግዚአብሔርም "እራቁትሀን መሆንህን ማን ነገረህ? `ከእርሱ እንዳትበላ` ብዬ ካዘዝሁህ ዛፍ በላህን?" አለው።
12፤ አዳምም አለ። ከእኔ ጋር እንድትሆን የሰጠኸኝ ሴት እርስዋ ከዛፉ ሰጠችኝና በላሁ።

13፤ እግዚአብሔር አምላክም ሴቲቱን። ይህ ያደረግሽው ምንድር ነው? አላት። ሴቲቱም አለች። እባብ አሳተኝና በላሁ።

14፤ እግዚአብሔር አምላክም እባቡን አለው። ይህን ስላደረግህ ከእንስሳት ከምድር አራዊትም ሁሉ ተለይተህ አንተ የተረገምህ ትሆናለህ፤ በሆድህም ትሄዳለህ፥ አፈርንም በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ትበላለህ።

15፤ በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ።

16፤ ለሴቲቱም አለ። በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤ ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፥ እርሱም ገዥሽ ይሆናል።

17፤ አዳምንም አለው። የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና፥ ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍም በልተሃልና ምድር ከአንተ የተነሣ የተረገመች ትሁን፤ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርስዋ ትበላለህ፤

18፤ እሾህንና አሜከላን ታበቅልብሃለች፤ የምድርንም ቡቃያ ትበላለህ።

19፤ ወደ ወጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ በፊትህ ወዝ እንጀራን ትበላለህ፤ አፈር ነህና፥ ወደ አፈርም ትመለሳለህና።

20፤ አዳምም ለሚስቱ ሔዋን ብሎ ስም አወጣ፥ የሕያዋን ሁሉ እናት ናትና።

21፤ እግዚአብሔር አምላክም ለአዳምና ለሚስቱ የቁርበትን ልብስ አደረገላቸው፥ አለበሳቸውም።

22፤ እግዚአብሔር አምላክም አለ። እነሆ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ፤ አሁንም እጁን እንዳይዘረጋ፥ ደግሞም ከሕይወት ዛፍ ወስዶ እንዳይበላ፥ ለዘላለምም ሕያው ሆኖ እንዳይኖር፤

23፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክ ከዔድን ገነት አስወጣው፥ የተገኘባትን መሬት ያርስ ዘንድ።

24፤ አዳምንም አስወጣው፥ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍን በዔድን ገነት ምሥራቅ አስቀመጠ።